#ይሳተፉ! #ይወዳደሩ! #ይሸለሙ!

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ጠቀሜታን የሚያስተዋዉቅ “ማስክ ኢትዮጽያ” ዘመቻ በክብርት የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ሰህለወርቅ ዘውዴ ይፋ ተደርጎ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። የጤና ሚኒስቴር ይህ ዘመቻ ከታለመለት ግብ ለማደረስም የሚመለከታቸው አካላት የማስክ አጠቃቀም የሚያስተምር፣ የሚሰጠውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በሚመለከት ግንዛቤን የሚፈጥር እና ሀገራዊ ዘመቻውን የሚያበረታታ የሰላሳ ሰከንድ የቪዲዮ እንዲሁም ፎቶግራፍ እና በሬዲዮ ሊቀርብ የሚችሉ ስራዎችን በማዘጋጀት እንዲሳተፉና ተወዳድሮ እንዲሸለሙ ይጋብዛል። በዚሁ መሰረት ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው moh@moh.gov.et እና maskethiopia@gmail.com ኢሜይል እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር ድህረገጽ ላይ በመግባት በተዘጋጀው ሙሉ መረጃ መሰረት እስከ ነሐሴ 18/2012 ዓ/ም ድረስ በመላክ ውድድሩን እንዲሳተፉ፣ ሀላፍነትዎን እንዲወጡ እንዲሁም ተወዳድሮ በማሸነፍ እንዲሸለሙ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ፡-
http://www.moh.gov.et/ejcc/am/Announcement

Leave A Reply

X